-
2 ዜና መዋዕል 6:28-30አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
28 “በምድሪቱ ላይ ረሃብ+ ወይም ቸነፈር፣+ የሚለበልብና የሚያደርቅ ነፋስ ወይም ዋግ+ ቢከሰት፣ የአንበጣ መንጋ ወይም የማይጠግብ አንበጣ*+ ቢመጣ አሊያም ጠላቶቻቸው በምድሪቱ ላይ ባለ በየትኛውም ከተማ* ውስጥ ሳሉ ቢከቧቸው+ ወይም ደግሞ ማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት አሊያም ማንኛውም ዓይነት በሽታ ቢከሰትና+ 29 ማንኛውም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል በሙሉ (እያንዳንዱ የገዛ ጭንቀቱንና ሥቃዩን ያውቃልና)+ ወደ አንተ ለመጸለይ+ ወይም ሞገስ እንድታሳየው ልመና ለማቅረብ+ እጁን ወደዚህ ቤት ቢዘረጋ+ 30 አንተ ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤+ ደግሞም ይቅር በል፤+ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው ብድራቱን ክፈለው፤ ምክንያቱም አንተ ልቡን ታውቃለህ (የሰውን ልብ በሚገባ የምታውቀው አንተ ብቻ ነህ)፤+
-