-
2 ዜና መዋዕል 24:24, 25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ወራሪው የሶርያ ሠራዊት አነስተኛ ቁጥር የነበረው ቢሆንም ይሖዋ እጅግ ብዙ የሆነውን ሠራዊት በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤+ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በመተዋቸው ነው፤ እነሱም* በኢዮዓስ ላይ የተላለፈውን ፍርድ ፈጸሙ። 25 እነሱም ጥለውት በሄዱ ጊዜ (ክፉኛ አቁስለውት* ነበርና) የገዛ አገልጋዮቹ የካህኑን የዮዳሄን ልጆች* ደም በማፍሰሱ አሴሩበት።+ አልጋው ላይ እንዳለ ገደሉት።+ ከሞተም በኋላ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤+ በነገሥታቱ የመቃብር ስፍራ ግን አልቀበሩትም።+
-
-
2 ዜና መዋዕል 28:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 በመጨረሻም አካዝ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ እነሱም በኢየሩሳሌም ከተማ ቀበሩት፤ ሆኖም የቀበሩት በእስራኤል ነገሥታት የመቃብር ስፍራ አልነበረም።+ በእሱም ምትክ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ።
-