24 በመጨረሻም ኢዮራም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ ከአባቶቹም ጋር በዳዊት ከተማ ተቀበረ።+ በእሱም ምትክ ልጁ አካዝያስ+ ነገሠ።
25 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በ12ኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ።+ 26 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ+ የተባለች የእስራኤል ንጉሥ የኦምሪ+ የልጅ ልጅ ነበረች።