1 ዜና መዋዕል 3:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የሰለሞን ልጅ ሮብዓም፣+ የሮብዓም ልጅ አቢያህ፣+ የአቢያህ ልጅ አሳ፣+ የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ፣+ 11 የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም፣+ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣+ የአካዝያስ ልጅ ኢዮዓስ፣+ 2 ዜና መዋዕል 21:16, 17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ከዚያም ይሖዋ ፍልስጤማውያንና+ በኢትዮጵያውያን አቅራቢያ የሚኖሩት ዓረቦች+ በኢዮራም ላይ እንዲነሱ አደረገ።*+ 17 እነሱም ይሁዳን ወረሩ፤ በኃይል ጥሰው በመግባትም በንጉሡ ቤት* ያገኙትን ንብረት ሁሉ+ እንዲሁም ልጆቹንና ሚስቶቹን ማርከው ወሰዱ፤ ከመጨረሻው ልጁ ከኢዮዓካዝ*+ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም። 2 ዜና መዋዕል 22:1, 2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ከዚያም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የመጨረሻ ልጁን አካዝያስን* በእሱ ምትክ አነገሡት፤ ከዓረቦቹ ጋር ወደ ሰፈሩ የመጡት ወራሪዎች ታላላቆቹን በሙሉ ገድለዋቸው ነበር።+ በመሆኑም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ።+ 2 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ+ የተባለች የኦምሪ+ የልጅ ልጅ* ነበረች።
10 የሰለሞን ልጅ ሮብዓም፣+ የሮብዓም ልጅ አቢያህ፣+ የአቢያህ ልጅ አሳ፣+ የአሳ ልጅ ኢዮሳፍጥ፣+ 11 የኢዮሳፍጥ ልጅ ኢዮራም፣+ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ፣+ የአካዝያስ ልጅ ኢዮዓስ፣+
16 ከዚያም ይሖዋ ፍልስጤማውያንና+ በኢትዮጵያውያን አቅራቢያ የሚኖሩት ዓረቦች+ በኢዮራም ላይ እንዲነሱ አደረገ።*+ 17 እነሱም ይሁዳን ወረሩ፤ በኃይል ጥሰው በመግባትም በንጉሡ ቤት* ያገኙትን ንብረት ሁሉ+ እንዲሁም ልጆቹንና ሚስቶቹን ማርከው ወሰዱ፤ ከመጨረሻው ልጁ ከኢዮዓካዝ*+ በቀር አንድም ልጅ አልቀረለትም።
22 ከዚያም የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የመጨረሻ ልጁን አካዝያስን* በእሱ ምትክ አነገሡት፤ ከዓረቦቹ ጋር ወደ ሰፈሩ የመጡት ወራሪዎች ታላላቆቹን በሙሉ ገድለዋቸው ነበር።+ በመሆኑም የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ጀመረ።+ 2 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው 22 ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሆኖ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም ጎቶልያ+ የተባለች የኦምሪ+ የልጅ ልጅ* ነበረች።