17 ከዚያም ዮዳሄ የይሖዋ ሕዝብ ሆነው እንዲቀጥሉ ይሖዋ፣ ንጉሡና ሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ፤+ በተጨማሪም ንጉሡና ሕዝቡ ቃል ኪዳን እንዲጋቡ አደረገ።+ 18 ከዚህም በኋላ የምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ ወደ ባአል ቤት መጥቶ መሠዊያዎቹን አፈራረሰ፤+ ምስሎቹንም እንክትክት አድርጎ ሰባበረ፤+ የባአል ካህን የነበረውን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ገደሉት።+
ከዚያም ካህኑ በይሖዋ ቤት ላይ የበላይ ተመልካቾችን ሾመ።+