12 ዳዊት በመንፈስ የተገለጠለትን የይሖዋን ቤት ቅጥር ግቢዎች፣+ በዙሪያው ያሉትን የመመገቢያ ክፍሎች ሁሉ፣ የእውነተኛውን አምላክ ቤት ግምጃ ቤቶችና የተቀደሱት ነገሮች+ የሚቀመጡባቸውን ግምጃ ቤቶች ንድፍ ሁሉ ለሰለሞን ሰጠው፤ 13 እንዲሁም የካህናቱንና+ የሌዋውያኑን ምድብ፣ በይሖዋ ቤት አገልግሎት የሚከናወነውን ሥራ ሁሉና በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት የሚውሉትን ዕቃዎች ሁሉ በተመለከተ መመሪያ ሰጠው፤