-
ነህምያ 10:38, 39አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
38 ሌዋውያኑ አንድ አሥረኛውን በሚቀበሉበት ጊዜ ካህኑ የአሮን ልጅ ከሌዋውያኑ ጋር አብሮ መሆን አለበት፤ ሌዋውያኑም የአንድ አሥረኛውን አንድ አሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት ይኸውም በግምጃ ቤቱ ውስጥ ወደሚገኙት ክፍሎች* መውሰድ ይኖርባቸዋል።+ 39 ምክንያቱም እስራኤላውያንም ሆኑ የሌዋውያኑ ልጆች የእህሉን፣ የአዲሱን ወይን ጠጅና የዘይቱን+ መዋጮ ማምጣት ያለባቸው ወደ ግምጃ ቤቶቹ* ነው፤+ ደግሞም የመቅደሱ ዕቃዎች የሚቀመጡትም ሆነ የሚያገለግሉት ካህናት፣ በር ጠባቂዎቹና ዘማሪዎቹ የሚገኙት በዚያ ነው። እኛም የአምላካችንን ቤት ቸል አንልም።+
-