-
ዘዳግም 32:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
“ክንዳችን የበላይ ሆነ፤+
ይህን ሁሉ ያደረገው ይሖዋ አይደለም” ሊሉ ይችላሉ።
-
-
ዳንኤል 3:14, 15አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ናቡከደነጾርም እንዲህ አላቸው፦ “ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ፣ አማልክቴን አለማገልገላችሁና+ ላቆምኩት የወርቅ ምስል አንሰግድም ማለታችሁ እውነት ነው? 15 አሁንም የቀንደ መለከት፣ የእምቢልታ፣ የተለያዩ ባለ አውታር መሣሪያዎች፣ የባለ ሦስት ማዕዘን በገና፣ የባለ ከረጢት ዋሽንትና የሌሎቹን የሙዚቃ መሣሪያዎች ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ ለሠራሁት ምስል ተደፍታችሁ ለመስገድ ፈቃደኞች ከሆናችሁ፣ መልካም! የማትሰግዱ ከሆነ ግን ወዲያውኑ ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ትጣላላችሁ። ለመሆኑ ከእጄ ሊያስጥላችሁ የሚችል አምላክ ማን ነው?”+
-