ዘሌዋውያን 2:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከእህል መባው የተረፈው ማንኛውም ነገር የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ነው፤+ ይህም ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች የተረፈ ስለሆነ እጅግ ቅዱስ ነው።+ ዘሌዋውያን 6:26 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 26 ይህን ለኃጢአት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ካህን ይበላዋል።+ በመገናኛ ድንኳኑ ግቢ ውስጥ ቅዱስ በሆነ ስፍራ ይበላል።+ ዘኁልቁ 18:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እስራኤላውያን ከሚወዘወዝ መባቸው+ ሁሉ ጋር መዋጮ አድርገው የሚያመጧቸው ስጦታዎች+ የአንተ ይሆናሉ። እነዚህን ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ።+ በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል።+
11 እስራኤላውያን ከሚወዘወዝ መባቸው+ ሁሉ ጋር መዋጮ አድርገው የሚያመጧቸው ስጦታዎች+ የአንተ ይሆናሉ። እነዚህን ለአንተ፣ ከአንተም ጋር ለወንዶች ልጆችህና ለሴቶች ልጆችህ ቋሚ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻችኋለሁ።+ በቤትህ ያለ ማንኛውም ንጹሕ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል።+