-
ዘዳግም 31:10-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “በየሰባት ዓመቱ መጨረሻ፣ በዓመቱ ውስጥ ዕዳ በሚሰረዝበት+ በተወሰነው ጊዜ ላይ ማለትም የዳስ* በዓል+ ሲከበር 11 መላው እስራኤል አምላክህ ይሖዋ በሚመርጠው ስፍራ በፊቱ በሚሰበሰብበት+ ጊዜ ይህን ሕግ እስራኤላውያን በሙሉ እንዲሰሙት አንብብላቸው።+ 12 ስለ አምላካችሁ ስለ ይሖዋ ይሰሙና ይማሩ እንዲሁም እሱን ይፈሩ ዘንድ ብሎም የዚህን ሕግ ቃላት በሙሉ በጥንቃቄ እንዲፈጽሙ ሕዝቡን ማለትም ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ልጆችንና* በከተሞችህ ውስጥ* የሚኖረውን የባዕድ አገር ሰው ሰብስብ።+
-