23 ከረጅም ጊዜ በኋላ የግብፁ ንጉሥ ሞተ፤+ እስራኤላውያን ግን ካሉበት የባርነት ሕይወት የተነሳ መቃተታቸውንና እሮሮ ማሰማታቸውን አላቆሙም ነበር፤ ከባርነት ሕይወታቸው የተነሳ እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙት ጩኸት ወደ እውነተኛው አምላክ ወጣ።+ 24 ከጊዜ በኋላም አምላክ በመቃተት የሚያሰሙትን ጩኸት አዳመጠ፤+ እንዲሁም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን አሰበ።+ 25 በመሆኑም አምላክ እስራኤላውያንን አየ፤ ያሉበትንም ሁኔታ ተመለከተ።