15 ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳትጋባ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም እነሱ አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር በሚፈጽሙበትና ለአማልክታቸው በሚሠዉበት+ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ አንተን መጋበዙ አይቀርም፣ አንተም ካቀረበው መሥዋዕት ትበላለህ።+ 16 ከዚያም ሴቶች ልጆቻቸውን ከወንዶች ልጆችህ ጋር ታጋባለህ፤+ ሴቶች ልጆቻቸውም አማልክታቸውን በማምለክ ምንዝር መፈጸማቸው እንዲሁም ወንዶች ልጆችህ የእነሱን አማልክት በማምለክ ምንዝር እንዲፈጽሙ ማድረጋቸው አይቀርም።+