-
ዘኁልቁ 22:4-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ስለዚህ ሞዓብ የምድያምን+ ሽማግሌዎች “በሬ በሜዳ ላይ ያለን ሣር ጠራርጎ እንደሚበላ ሁሉ ይህም ጉባኤ በዙሪያችን ያለውን ሁሉ ጠራርጎ ያጠፋል” አላቸው።
በዚያን ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ የሞዓብ ንጉሥ ነበር። 5 እሱም የቢዖርን ልጅ በለዓምን እንዲጠሩት መልእክተኞችን ላከ፤ በለዓም የሚኖረው በትውልድ አገሩ ባለው ወንዝ* ዳር በምትገኘው በጰቶር ነበር።+ እንዲህም ብለው እንዲነግሩት ላካቸው፦ “ከግብፅ ወጥቶ የመጣ አንድ ሕዝብ አለ። ይኸው የምድሪቱን* ገጽ* ሸፍኗል፤+ ደግሞም መጥቶ አፍንጫዬ ሥር ሰፍሯል። 6 እነሱ ከእኔ ይልቅ ኃያላን ስለሆኑ እባክህ መጥተህ ይህን ሕዝብ እርገምልኝ።+ ምናልባትም ድል አድርጌ ከምድሪቱ ላባርራቸው እችላለሁ፤ ምክንያቱም አንተ የባረክኸው ሁሉ የተባረከ፣ የረገምከውም ሁሉ የተረገመ እንደሚሆን በሚገባ አውቃለሁ።”
-