-
አስቴር 9:1, 2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 አዳር* በተባለው በ12ኛው ወር፣ 13ኛ ቀን፣+ የንጉሡ ቃልና ሕግ በሚፈጸምበት+ እንዲሁም የአይሁዳውያን ጠላቶች በአይሁዳውያን ላይ ድል እንደሚቀዳጁ ተስፋ አድርገው በነበረበት ቀን ነገሩ የተገላቢጦሽ ሆነ፤ አይሁዳውያኑ የሚጠሏቸውን ሰዎች ድል አደረጉ።+ 2 አይሁዳውያኑ እነሱን ለመጉዳት በሚሹ ሰዎች ላይ እጃቸውን ለማንሳት በንጉሥ አሐሽዌሮስ+ አውራጃዎች በሙሉ በሚገኙ ከተሞቻቸው ውስጥ ተሰባሰቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ፈርቷቸው ስለነበር ሊቃወማቸው የቻለ አንድም ሰው አልነበረም።+
-