መዝሙር 58:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በዚህ ጊዜ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፦ “በእርግጥ ጻድቁ ብድራት ይቀበላል።+ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ።”+ ማቴዎስ 7:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 “እንዳይፈረድባችሁ በሌሎች ላይ አትፍረዱ፤*+ ሮም 14:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በሌላው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?+ እሱ ቢቆምም ሆነ ቢወድቅ ለጌታው ነው።+ እንዲያውም ይሖዋ* እንዲቆም ሊያደርገው ስለሚችል ይቆማል። ያዕቆብ 4:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ሕግ የሚሰጥና የሚፈርድ አንድ ብቻ ነው፤+ እሱ ማዳንም ሆነ ማጥፋት ይችላል።+ ታዲያ በባልንጀራህ* ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?+