መዝሙር 11:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በክፉዎች ላይ ወጥመድ* ያዘንባል፤እሳትና ድኝ+ እንዲሁም የሚለበልብ ነፋስ ጽዋቸው ይሆናል። መክብብ 8:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ክፉ ሰው ግን አምላክን ስለማይፈራ የኋላ ኋላ መልካም አይሆንለትም፤+ እንደ ጥላ የሆነውን የሕይወት ዘመኑንም ማራዘም አይችልም።+ ሚልክያስ 3:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ለመፍረድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በመተተኞቹ፣+ በአመንዝሮቹ፣ በሐሰት በሚምሉት ሰዎች+ እንዲሁም ቅጥር ሠራተኛውን፣+ መበለቲቱንና አባት የሌለውን ልጅ* በሚያጭበረብሩትና+ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ በማይሆኑት* ላይ ወዲያውኑ እመሠክርባቸዋለሁ።+ እነዚህ ሰዎች እኔን አልፈሩም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
5 “ለመፍረድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በመተተኞቹ፣+ በአመንዝሮቹ፣ በሐሰት በሚምሉት ሰዎች+ እንዲሁም ቅጥር ሠራተኛውን፣+ መበለቲቱንና አባት የሌለውን ልጅ* በሚያጭበረብሩትና+ ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ በማይሆኑት* ላይ ወዲያውኑ እመሠክርባቸዋለሁ።+ እነዚህ ሰዎች እኔን አልፈሩም” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።