-
ዘፍጥረት 38:24አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
24 ይሁን እንጂ ከሦስት ወር በኋላ ለይሁዳ “ምራትህ ትዕማር ዝሙት አዳሪ ሆናለች፤ ዝሙት በመፈጸሟም ፀንሳለች” ተብሎ ተነገረው። በዚህ ጊዜ ይሁዳ “አውጧትና በእሳት ትቃጠል” አለ።+
-
-
ዘሌዋውያን 20:10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 “‘ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽምን ሰው በተመለከተ እንዲህ ይደረግ፦ ከባልንጀራው ሚስት ጋር ምንዝር የሚፈጽም ሰው ይገደል፤ አመንዝራውም ሆነ አመንዝራይቱ ይገደሉ።+
-
-
ዘዳግም 22:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ከሴትየዋ ጋር የተኛው ሰውም ሆነ ሴትየዋ ሁለቱም ይገደሉ።+ በዚህ መንገድ ክፉ የሆነውን ከእስራኤል መካከል አስወግድ።
-