ዘፍጥረት 1:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ምድርም ቅርጽ አልባና ባድማ ነበረች፤* ጥልቁም* ውኃ+ በጨለማ ተሸፍኖ ነበር፤ የአምላክም ኃይል*+ በውኃው ላይ ይንቀሳቀስ ነበር።+ መዝሙር 77:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 መንገድህ በባሕር ውስጥ ነበር፤+ጎዳናህም በብዙ ውኃዎች ውስጥ ነበር፤ይሁንና የእግርህ ዱካ ሊገኝ አልቻለም።