-
ዘፍጥረት 18:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 ለይሖዋ የሚሳነው ነገር አለ?+ የዛሬ ዓመት በዚሁ በተወሰነው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ወንድ ልጅ ትወልዳለች።”
-
-
መዝሙር 135:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 በሰማይና በምድር፣ በባሕሮችና በጥልቆች ውስጥ
ይሖዋ ደስ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።+
-
-
ኢሳይያስ 43:13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
እርምጃ በምወስድበት ጊዜ ሊያግድ የሚችል ማን ነው?”+
-
-
ኤርምያስ 32:17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
17 “አቤቱ፣ ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ! እነሆ፣ አንተ ሰማያትንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ሠርተሃል።+ አንተ ምንም የሚሳንህ ነገር የለም፤
-
-
ማርቆስ 10:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን ትኩር ብሎ በመመልከት “ይህ በሰዎች ዘንድ አይቻልም፤ በአምላክ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም፤ በአምላክ ዘንድ ሁሉ ነገር ይቻላል” አለ።+
-
-
ሉቃስ 18:27አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 እሱም “በሰዎች ዘንድ የማይቻል፣ በአምላክ ዘንድ ይቻላል” አለ።+
-