መዝሙር
135 ያህን አወድሱ!*
3 ይሖዋ ጥሩ ነውና፣+ ያህን አወድሱ።
ደስ የሚያሰኝ ነውና፣ ለስሙ የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።
5 ይሖዋ ታላቅ መሆኑን በሚገባ አውቃለሁና፤
ጌታችን ከሌሎች አማልክት ሁሉ የላቀ ነው።+
6 በሰማይና በምድር፣ በባሕሮችና በጥልቆች ውስጥ
ይሖዋ ደስ ያሰኘውን ነገር ሁሉ ያደርጋል።+
8 በግብፅ የተወለደውን
የሰውም ሆነ የእንስሳ በኩር ገደለ።+
12 ምድራቸውን ርስት አድርጎ፣
አዎ፣ ርስት አድርጎ ለሕዝቡ ለእስራኤል ሰጠ።+
13 ይሖዋ ሆይ፣ ስምህ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ይሖዋ ሆይ፣ ዝናህ* ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዘልቃል።+
15 የብሔራት ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣
የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+
በአፋቸው ውስጥ እስትንፋስ የለም።+
19 የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።
የአሮን ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።
20 የሌዊ ቤት ሆይ፣ ይሖዋን አወድሱ።+
እናንተ ይሖዋን የምትፈሩ፣ ይሖዋን አወድሱ።
ያህን አወድሱ!+