የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 115:4-8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 የእነሱ ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣

      የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+

       5 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+

      ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤

       6 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም፤

      አፍንጫ አላቸው፤ ማሽተት ግን አይችሉም፤

       7 እጅ አላቸው፤ መዳሰስ ግን አይችሉም፤

      እግር አላቸው፤ መራመድ ግን አይችሉም፤+

      በጉሮሯቸው የሚያሰሙት ድምፅ የለም።+

       8 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣

      እንደ እነሱ ይሆናሉ።+

  • ኢሳይያስ 46:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ከኮሮጇቸው ወርቅ የሚዘረግፉ ሰዎች አሉ፤

      ብሩን በሚዛን ይመዝናሉ።

      አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ እሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል።+

      እነሱም በፊቱ ይደፋሉ፤ ደግሞም ያመልኩታል።*+

  • የሐዋርያት ሥራ 17:29
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 29 “እንግዲህ እኛ የአምላክ ልጆች+ ከሆንን አምላክ በሰው ጥበብና ንድፍ ከወርቅ፣ ከብር ወይም ከድንጋይ የተቀረጸን ነገር ይመስላል ብለን ልናስብ አይገባም።+

  • 1 ቆሮንቶስ 10:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 እንግዲህ ምን እያልኩ ነው? ለጣዖት የተሠዋ ነገር የተለየ ፋይዳ አለው ማለቴ ነው? ወይስ ጣዖት ዋጋ አለው ማለቴ ነው?

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ