የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መዝሙር 135:15-18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 የብሔራት ጣዖቶች ከብርና ከወርቅ የተሠሩ፣

      የሰው እጅ ሥራ ናቸው።+

      16 አፍ አላቸው፤ መናገር ግን አይችሉም፤+

      ዓይን አላቸው፤ ማየት ግን አይችሉም፤

      17 ጆሮ አላቸው፤ መስማት ግን አይችሉም።

      በአፋቸው ውስጥ እስትንፋስ የለም።+

      18 የሚሠሯቸውም ሆኑ የሚታመኑባቸው ሁሉ፣+

      እንደ እነሱ ይሆናሉ።+

  • ኢሳይያስ 40:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 የእጅ ጥበብ ባለሙያ ብረት አቅልጦ ጣዖት* ይሠራል፤

      አንጥረኛውም በወርቅ ይለብጠዋል፤+

      የብር ሰንሰለትም ይሠራለታል።

  • ኢሳይያስ 46:6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  6 ከኮሮጇቸው ወርቅ የሚዘረግፉ ሰዎች አሉ፤

      ብሩን በሚዛን ይመዝናሉ።

      አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ እሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል።+

      እነሱም በፊቱ ይደፋሉ፤ ደግሞም ያመልኩታል።*+

  • ኤርምያስ 10:3, 4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 የእነዚህ ሕዝቦች ልማድ ከንቱ* ነውና፤

      የእጅ ጥበብ ባለሙያ ዛፍ ከጫካ ይቆርጥና

      በመሣሪያው* ጠርቦ ጣዖት ይሠራል።+

       4 በብርና በወርቅ ያስጌጡታል፤+

      እንዳይወድቅም በመዶሻና በምስማር ይቸነክሩታል።+

  • ኤርምያስ 10:8, 9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  8 ሁሉም የማመዛዘን ችሎታ የጎደላቸውና ሞኞች ናቸው።+

      ከእንጨት ምስል የሚመጣ መመሪያ ፈጽሞ ከንቱ* ነው።+

       9 በእጅ ጥበብ ባለሙያና በአንጥረኛ የተሠራ

      የተጠፈጠፈ ብር ከተርሴስ፣+ ወርቅም ከዑፋዝ ይመጣል።

      ልብሳቸው በሰማያዊ ክርና በሐምራዊ ሱፍ የተሠራ ነው።

      ሁሉም በባለሙያዎች የተሠሩ ናቸው።

  • የሐዋርያት ሥራ 19:26
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 26 አሁን ግን ይህ ጳውሎስ የተባለ ሰው በኤፌሶን+ ብቻ ሳይሆን በመላው የእስያ አውራጃ ማለት ይቻላል፣ በእጅ የተሠሩ አማልክት ሁሉ በፍጹም አማልክት አይደሉም እያለ ብዙ ሰዎችን አሳምኖ አመለካከታቸውን እንዳስለወጠ ያያችሁትና የሰማችሁት ጉዳይ ነው።+

  • 1 ቆሮንቶስ 10:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 እንግዲህ ምን እያልኩ ነው? ለጣዖት የተሠዋ ነገር የተለየ ፋይዳ አለው ማለቴ ነው? ወይስ ጣዖት ዋጋ አለው ማለቴ ነው?

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ