ኢሳይያስ 40:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አንድ ሰው መዋጮ አድርጎ ለመስጠትየማይበሰብስ ዛፍ ይመርጣል።+ የማይወድቅ ምስል ቀርጾ እንዲያዘጋጅለትበእጅ ጥበብ ሥራ የተካነ ባለሙያ ይፈልጋል።+ ኢሳይያስ 44:14, 15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 አርዘ ሊባኖስ የሚቆርጥ ሰው አለ። እሱም አንድ የዛፍ ዝርያ ይኸውም የባሉጥ ዛፍ ይመርጣል፤እስኪጠነክርለት ድረስ በጫካው ውስጥ ባሉት ዛፎች መካከል ይተወዋል።+ የላውሮ ዛፍ ይተክላል፤ ዝናብም ያሳድገዋል። 15 ከዚያም ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል። የተወሰነውን እንጨት ወስዶ በማንደድ እሳት ይሞቃል፤እሳት አያይዞም ዳቦ ይጋግራል። ይሁንና አምላክ ሠርቶም ያመልከዋል። የተቀረጸ ምስል ሠርቶበት በፊቱ ይደፋል።+ ኢሳይያስ 45:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ተሰብስባችሁ ኑ። እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ።+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ+ ምንም እውቀት የላቸውም። ዕንባቆም 2:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+
14 አርዘ ሊባኖስ የሚቆርጥ ሰው አለ። እሱም አንድ የዛፍ ዝርያ ይኸውም የባሉጥ ዛፍ ይመርጣል፤እስኪጠነክርለት ድረስ በጫካው ውስጥ ባሉት ዛፎች መካከል ይተወዋል።+ የላውሮ ዛፍ ይተክላል፤ ዝናብም ያሳድገዋል። 15 ከዚያም ሰው ለማገዶ ይጠቀምበታል። የተወሰነውን እንጨት ወስዶ በማንደድ እሳት ይሞቃል፤እሳት አያይዞም ዳቦ ይጋግራል። ይሁንና አምላክ ሠርቶም ያመልከዋል። የተቀረጸ ምስል ሠርቶበት በፊቱ ይደፋል።+
20 ተሰብስባችሁ ኑ። እናንተ ከብሔራት ያመለጣችሁ፣ በአንድነት ቅረቡ።+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውን ተሸክመው የሚዞሩም ሆኑሊያድናቸው ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ+ ምንም እውቀት የላቸውም።
18 የተቀረጸ ምስል፣ሠሪው የቀረጸው ከሆነ ምን ጥቅም አለው? ሠሪው እምነት ቢጥልበትም እንኳከብረት የተሠራ ሐውልትና* ሐሰትን የሚናገር አስተማሪ ምን ፋይዳ አለው?መናገር የማይችሉ ከንቱ አማልክት መሥራት ምን እርባና አለው?+