-
ዘኁልቁ 21:33-35አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
33 ከዚህ በኋላ ተመልሰው በባሳን መንገድ ወጡ። የባሳን ንጉሥ ኦግም+ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር በመሆን ኤድራይ ላይ ጦርነት ሊገጥማቸው ወጣ።+ 34 ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እሱንም ሆነ ሕዝቡን ሁሉ እንዲሁም ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ስለምሰጥህ አትፍራው፤+ አንተም በሃሽቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሲሖን ላይ እንዳደረግከው በእሱም ላይ ታደርግበታለህ።”+ 35 በመሆኑም ኦግን ከወንዶች ልጆቹና ከሕዝቡ ሁሉ ጋር አንድም ሰው ሳያስቀሩ ሁሉንም ደመሰሱ፤+ ምድሩንም ወረሱ።+
-