-
መዝሙር 107:29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 አውሎ ነፋሱ እንዲቆም ያደርጋል፤
የባሕሩም ሞገዶች ጸጥ ይላሉ።+
-
-
ኢሳይያስ 17:12, 13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 አዳምጡ! እንደሚናወጥ ባሕር ያለ
የብዙ ሕዝቦች ትርምስ ይሰማል!
እንደ ኃይለኛ ውኃዎች ድምፅ ያለ
የሚያስገመግም የብሔራት ጫጫታ ይሰማል!
13 ብሔራት እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ያለ የሚያስገመግም ድምፅ ያሰማሉ።
እሱ ይገሥጻቸዋል፤ እነሱም ወደ ሩቅ ቦታ ይሸሻሉ፤
በተራራ ላይ እንዳለ በነፋስ እንደሚበን ገለባና
አውሎ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ ይሆናሉ።
-
-
ኢሳይያስ 57:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 “ክፉዎች ግን ጸጥ ማለት እንደማይችል የሚናወጥ ባሕር ናቸው፤
ውኃውም የባሕር ውስጥ ዕፀዋትንና ጭቃን ያወጣል።
-