ዘሌዋውያን 26:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ዝናብን በወቅቱ አዘንብላችኋለሁ፤+ ምድሪቱም ምርቷን ትሰጣለች፤+ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጣሉ። መዝሙር 85:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 አዎ፣ ይሖዋ መልካም ነገር* ይሰጣል፤+ምድራችንም ምርቷን ትሰጣለች።+ ኢሳይያስ 30:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 እሱም መሬት ላይ ለምትዘራው ዘር ዝናብ ይሰጥሃል፤+ ምድሪቱም የምታፈራው እህል የተትረፈረፈና ምርጥ* ይሆናል።+ በዚያም ቀን ከብቶችህ ሰፊ በሆነ የግጦሽ መስክ ይሰማራሉ።+ ሕዝቅኤል 34:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 የሜዳው ዛፎች ፍሬያቸውን ይሰጣሉ፤ መሬቱም ፍሬ ይሰጣል፤+ እነሱም በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ። ቀንበራቸውን በምሰብርበትና ባሪያ አድርገው ከሚገዟቸው እጅ በማድናቸው ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+
23 እሱም መሬት ላይ ለምትዘራው ዘር ዝናብ ይሰጥሃል፤+ ምድሪቱም የምታፈራው እህል የተትረፈረፈና ምርጥ* ይሆናል።+ በዚያም ቀን ከብቶችህ ሰፊ በሆነ የግጦሽ መስክ ይሰማራሉ።+
27 የሜዳው ዛፎች ፍሬያቸውን ይሰጣሉ፤ መሬቱም ፍሬ ይሰጣል፤+ እነሱም በምድሪቱ ላይ ያለስጋት ይቀመጣሉ። ቀንበራቸውን በምሰብርበትና ባሪያ አድርገው ከሚገዟቸው እጅ በማድናቸው ጊዜ እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ።+