መዝሙር 22:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ችግር ሊደርስብኝ ስለሆነ ከእኔ አትራቅ፤+ደግሞም ሌላ ረዳት የለኝም።+ መዝሙር 35:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ይሖዋ ሆይ፣ ይህን ተመልክተሃል። ዝም አትበል።+ ይሖዋ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ መዝሙር 38:21, 22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 ይሖዋ ሆይ፣ አትተወኝ። አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ።+ 22 አዳኜ ይሖዋ ሆይ፣እኔን ለመርዳት ፍጠን።+