ዘፀአት 15:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 አዳኜ ስለሆነልኝ ያህ* ብርታቴና ኃይሌ ነው።+ እሱ አምላኬ ነው፤ አወድሰዋለሁ፤+ የአባቴ አምላክ ነው፤+ እኔም ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።+ ኢሳይያስ 33:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ይሖዋ ዳኛችን ነው፤+ይሖዋ ሕግ ሰጪያችን ነው፤+ይሖዋ ንጉሣችን ነው፤+የሚያድነን እሱ ነው።+