1 ዜና መዋዕል 16:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤+አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።*+ መዝሙር 143:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 የጥንቱን ዘመን አስታውሳለሁ፤ባከናወንካቸው ነገሮች ሁሉ ላይ አሰላስላለሁ፤+የእጆችህን ሥራ በታላቅ ጉጉት አውጠነጥናለሁ።*