ዘፀአት 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤+ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ።+ 2 ሳሙኤል 22:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ምድርም ወዲያና ወዲህ ትናወጥና ትንቀጠቀጥ ጀመር፤+የሰማያት መሠረቶች ተንቀጠቀጡ፤+እሱ ስለተቆጣም ራዱ።+