ዘፀአት 15:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ጠላትም ‘አሳድዳቸዋለሁ! አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ! እስክጠግብም* ድረስ ምርኮን እከፋፈላለሁ! ሰይፌን እመዛለሁ! እጄም ታንበረክካቸዋለች!’ አለ።+ 10 አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤+ እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ። 1 ሳሙኤል 2:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በትዕቢት መናገራችሁን ተዉ፤የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፣ይሖዋ ሁሉን የሚያውቅ አምላክ ነውና፣+ተግባርን ሁሉ በትክክል የሚመዝን እሱ ነው። ሕዝቅኤል 28:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልብህ ከመታበዩ የተነሳ+ ‘እኔ አምላክ ነኝ። በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ።+ በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንምአንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።
9 ጠላትም ‘አሳድዳቸዋለሁ! አሳድጄ እደርስባቸዋለሁ! እስክጠግብም* ድረስ ምርኮን እከፋፈላለሁ! ሰይፌን እመዛለሁ! እጄም ታንበረክካቸዋለች!’ አለ።+ 10 አንተም እስትንፋስህን እፍ አልክ፤ ባሕሩም ከደናቸው፤+ እነሱም ኃያል በሆኑ ውኃዎች ውስጥ እንደ አረር ሰመጡ።
2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “ልብህ ከመታበዩ የተነሳ+ ‘እኔ አምላክ ነኝ። በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ።+ በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንምአንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።