-
ዘፀአት 1:8-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብፅ ተነሳ። 9 እሱም ሕዝቦቹን እንዲህ አላቸው፦ “ይኸው እንደምታዩት የእስራኤል ሕዝብ ከእኛ ይልቅ እጅግ ብዙና ኃያል ነው።+ 10 እንግዲህ እነሱን በተመለከተ አንድ መላ እንፍጠር። ካልሆነ ግን ቁጥራቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ደግሞም ጦርነት ከተነሳ ከጠላቶቻችን ጋር ወግነው እኛን መውጋታቸውና አገሪቱን ጥለው መኮብለላቸው አይቀርም።”
-
-
አስቴር 3:6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ሆኖም ስለ መርዶክዮስ ወገኖች ነግረውት ስለነበር መርዶክዮስን ብቻ ማስገደሉ* ተራ ነገር እንደሆነ ተሰማው። ስለዚህ ሃማ በመላው የአሐሽዌሮስ ግዛት የሚገኙትን አይሁዳውያን በሙሉ ማለትም የመርዶክዮስን ወገኖች በአጠቃላይ ለማጥፋት ዘዴ ይፈልግ ጀመር።
-