ዘፀአት 6:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሁሉን ቻይ አምላክ+ ሆኜ እገለጥላቸው ነበር፤ ይሖዋ የሚለውን ስሜን+ በተመለከተ ግን ራሴን ሙሉ በሙሉ አልገለጥኩላቸውም።+ መዝሙር 68:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ለአምላክ ዘምሩ፤ ለስሙም የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ።+ በበረሃማ ሜዳዎች* እየጋለበ ለሚያቋርጠው ለእሱ ዘምሩ። ስሙ ያህ* ነው!+ በፊቱ እጅግ ደስ ይበላችሁ! ኢሳይያስ 42:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ኢሳይያስ 54:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ታላቁ ሠሪሽ+ ባልሽ* ነውና፤+ስሙም የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ነው፤የሚቤዥሽም+ የእስራኤል ቅዱስ ነው። እሱም የምድር ሁሉ አምላክ ተብሎ ይጠራል።+