የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 16:8-13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 “ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤

      ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+

      9 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤+

      አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።*+

      10 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+

      ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+

      11 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+

      ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።+

      12 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣

      ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+

      13 እናንተ የአገልጋዩ የእስራኤል ዘሮች፣+

      እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።

  • መዝሙር 96:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  3 ክብሩን በብሔራት፣

      አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።+

  • መዝሙር 145:11, 12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 የንግሥናህን ክብር ያውጃሉ፤+

      ስለ ኃያልነትህም ይናገራሉ፤+

      ל [ላሜድ]

      12 ይህም ለሰዎች ታላላቅ ሥራዎችህንና+

      የንግሥናህን ታላቅ ክብር+ ያስታውቁ ዘንድ ነው።

  • ኢሳይያስ 12:4
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፦

      “ይሖዋን አመስግኑ! ስሙን ጥሩ፤

      ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+

      ስሙ ከፍ ከፍ ማለቱን አውጁ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ