የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 12:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ።

  • ዘፍጥረት 13:14, 15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 ሎጥ ከአብራም ከተለየ በኋላ ይሖዋ አብራምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ካለህበት ቦታ ሆነህ ዓይንህን አቅንተህ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ተመልከት፤ 15 ምክንያቱም የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘለቄታው ርስት አድርጌ እሰጣለሁ።+

  • ዘፍጥረት 15:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 በዚያ ቀን ይሖዋ እንዲህ ሲል ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገባ፦+ “ከግብፅ ወንዝ አንስቶ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ+ ድረስ ያለውን ይህን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤+

  • ዘፍጥረት 26:3
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 3 በዚህ ምድር እንደ ባዕድ አገር ሰው ሆነህ ተቀመጥ፤+ እኔም ከአንተ ጋር መሆኔን እቀጥላለሁ፤ እንዲሁም እባርክሃለሁ። ምክንያቱም ይህችን ምድር በሙሉ ለአንተና ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤+ ደግሞም ለአባትህ ለአብርሃም እንዲህ ስል የማልሁለትን መሐላ እፈጽማለሁ፦+

  • ዘፍጥረት 28:13
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 13 ከደረጃውም በላይ ይሖዋ ነበር፤ እሱም እንዲህ አለ፦

      “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክና የይስሐቅ አምላክ ይሖዋ ነኝ።+ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።+

  • መዝሙር 78:55
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 55 ብሔራቱን ከፊታቸው አባረረ፤+

      በመለኪያ ገመድም ርስት አከፋፈላቸው፤+

      የእስራኤልን ነገዶች በቤቶቻቸው እንዲኖሩ አደረገ።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ