ሩት 2:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ላደረግሽው ሁሉ ይሖዋ ብድራትሽን ይመልስልሽ፤+ በክንፎቹ ሥር ለመጠለል+ ብለሽ ወደ እሱ የመጣሽበት የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ሙሉ ዋጋሽን* ይክፈልሽ።” መዝሙር 36:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!+ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።+ መዝሙር 57:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 57 ሞገስ አሳየኝ፤ አምላክ ሆይ፣ ሞገስ አሳየኝ፤አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፤*+መከራው እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ ሥር እጠለላለሁ።+