-
ዘኁልቁ 25:11-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 “የካህኑ የአሮን ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ ፊንሃስ+ በመካከላቸው እኔን የሚቀናቀነኝን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ ቁጣዬ ከእስራኤል ሕዝብ ላይ እንዲመለስ አድርጓል።+ ስለዚህ እስራኤላውያንን እኔን ብቻ ለምን አላመለካችሁም ብዬ ጠራርጌ አላጠፋኋቸውም።+ 12 በዚህም የተነሳ ከእሱ ጋር የሰላም ቃል ኪዳን እንደምገባ ንገረው። 13 ይህም አምላኩን የሚቀናቀነውን ማንኛውንም ነገር በቸልታ ባለማለፉ+ እንዲሁም ለእስራኤል ሕዝብ በማስተሰረዩ ለእሱና ከእሱ በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ+ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ሆኖ ያገለግላል።”
-