-
መሳፍንት 10:6-8አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 እስራኤላውያንም በይሖዋ ፊት እንደገና መጥፎ ነገር አደረጉ፤+ ባአልን፣+ የአስታሮትን ምስሎች፣ የአራምን* አማልክት፣ የሲዶናን አማልክት፣ የሞዓብን አማልክት፣+ የአሞናውያንን አማልክትና+ የፍልስጤማውያንን አማልክት+ ማገልገል ጀመሩ። ይሖዋን ተዉት፤ እሱንም አላገለገሉም። 7 የይሖዋም ቁጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፤ እነሱንም ለፍልስጤማውያንና ለአሞናውያን ሸጣቸው።+ 8 ስለሆነም በዚያ ዓመት እስራኤላውያንን አደቀቋቸው፤ ክፉኛም ጨቆኗቸው፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ በጊልያድ በሚገኘው በአሞራውያን ምድር የነበሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ለ18 ዓመት ጨቆኗቸው።
-