ዘፀአት 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤+ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ።+ መሳፍንት 5:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ከሴይር+ በወጣህ ጊዜ፣ከኤዶም ክልል እየገሰገስክ በመጣህ ጊዜ፣ምድር ተናወጠች፤ ሰማያትም ውኃ አወረዱ፤ደመናትም ውኃ አንዠቀዠቁ።