መዝሙር 25:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የይሖዋ መንገዶች ሁሉ፣ ቃል ኪዳኑንና+ ማሳሰቢያዎቹን+ ለሚጠብቁ፣ታማኝ ፍቅር የሚንጸባረቅባቸውና እምነት የሚጣልባቸው ናቸው። መዝሙር 91:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 በላባዎቹ ይከልልሃል፤*በክንፎቹም ሥር መጠጊያ ታገኛለህ።+ ታማኝነቱ+ ትልቅ ጋሻና+ መከላከያ ቅጥር* ይሆንልሃል።