1 ሳሙኤል 1:10, 11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 እሷም በጣም ተማርራ* ነበር፤ ስቅስቅ ብላም እያለቀሰች ወደ ይሖዋ ትጸልይ ጀመር።+ 11 እንዲህም ስትል ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ እየደረሰባት ያለውን መከራ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት+ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለይሖዋ እሰጠዋለሁ፤ ራሱንም ምላጭ አይነካውም።”+ 2 ሳሙኤል 16:11, 12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፦ “ከአብራኬ የወጣው የገዛ ልጄ እንኳ ይኸው ሕይወቴን* እየፈለገ አይደል?+ ታዲያ አንድ ቢንያማዊ+ እንዲህ ቢያደርግ ምን ያስደንቃል! ተዉት ይርገመኝ፤ ይሖዋ እርገመው ብሎት ነው! 12 ምናልባትም ይሖዋ መከራዬን ያይልኝና+ በዛሬው እርግማን ፋንታ ይሖዋ መልካም ነገር ያደርግልኝ ይሆናል።”+ ኢሳይያስ 38:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከዳነ በኋላ የጻፈው* ጽሑፍ፦ ኢሳይያስ 38:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 ይሖዋ ሆይ፣ አድነኝ፤በሕይወታችን ዘመን ሁሉ በይሖዋ ቤት፣+በባለ አውታር መሣሪያዎች መዝሙሮቼን እንዘምራለን።’”+
10 እሷም በጣም ተማርራ* ነበር፤ ስቅስቅ ብላም እያለቀሰች ወደ ይሖዋ ትጸልይ ጀመር።+ 11 እንዲህም ስትል ተሳለች፦ “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ አገልጋይህ እየደረሰባት ያለውን መከራ ተመልክተህ ብታስበኝና አገልጋይህን ሳትረሳት ወንድ ልጅ ብትሰጣት+ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለይሖዋ እሰጠዋለሁ፤ ራሱንም ምላጭ አይነካውም።”+
11 ከዚያም ዳዊት አቢሳንና አገልጋዮቹን በሙሉ እንዲህ አላቸው፦ “ከአብራኬ የወጣው የገዛ ልጄ እንኳ ይኸው ሕይወቴን* እየፈለገ አይደል?+ ታዲያ አንድ ቢንያማዊ+ እንዲህ ቢያደርግ ምን ያስደንቃል! ተዉት ይርገመኝ፤ ይሖዋ እርገመው ብሎት ነው! 12 ምናልባትም ይሖዋ መከራዬን ያይልኝና+ በዛሬው እርግማን ፋንታ ይሖዋ መልካም ነገር ያደርግልኝ ይሆናል።”+