1 ዜና መዋዕል 29:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ከዚህም በላይ ለአምላኬ ቤት ካለኝ ፍቅር+ የተነሳ ለቅዱሱ ቤት አስቀድሞ ካዘጋጀሁት በተጨማሪ የግል ሀብቴ+ የሆነውን ወርቅና ብርም ለአምላኬ ቤት እሰጣለሁ፤ መዝሙር 26:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሖዋ ሆይ፣ የምትኖርበትን ቤት፣+የክብርህንም ማደሪያ ቦታ እወዳለሁ።+ መዝሙር 69:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ለቤትህ ያለኝ ቅንዓት በልቶኛል፤+ሰዎች አንተን ይነቅፉበት የነበረው ነቀፋም በእኔ ላይ ደረሰ።+