መዝሙር 6:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በሐዘኔ ምክንያት ዓይኔ ደክሟል፤+ከሚያጠቁኝ ሰዎች ሁሉ የተነሳ ዓይኔ ፈዟል።* መዝሙር 22:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 እንደ ውኃ ፈሰስኩ፤አጥንቶቼ ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ። ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤+በውስጤም ቀለጠ።+