መዝሙር 62:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 62 ዝም ብዬ አምላክን እጠባበቃለሁ።* መዳን የማገኘው ከእሱ ዘንድ ነው።+ ሰቆቃወ ኤርምያስ 3:20, 21 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 አንተ በእርግጥ ታስታውሳለህ፤* እኔን ለመርዳትም ታጎነብሳለህ።+ 21 ይህ ከልቤ አይጠፋም፤ ከዚህም የተነሳ በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።+ ሚክያስ 7:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 እኔ ግን ይሖዋን በጉጉት እጠባበቃለሁ።+ የሚያድነኝን አምላክ በትዕግሥት እጠብቃለሁ።*+ አምላኬ ይሰማኛል።+