2 ነገሥት 7:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ምክንያቱም ይሖዋ የሶርያውያን ሰፈር የጦር ሠረገሎችን ድምፅ፣ የፈረሶችን ድምፅና የታላቅ ሠራዊት ድምፅ እንዲሰማ አድርጎ ነበር።+ በመሆኑም እርስ በርሳቸው “የእስራኤል ንጉሥ እኛን ለመውጋት የሂታውያንንና የግብፅን ነገሥታት ቀጥሮብናል!” ተባባሉ። 7 እነሱም ወዲያውኑ ተነስተው በምሽት ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም ሰፈሩን እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን* ለማዳን እግሬ አውጪኝ አሉ። መዝሙር 20:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አንዳንዶች በሠረገሎች፣ ሌሎች ደግሞ በፈረሶች ይታመናሉ፤+እኛ ግን የአምላካችንን የይሖዋን ስም እንጠራለን።+ ምሳሌ 21:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፤+መዳን ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።+ ኢሳይያስ 31:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 እርዳታ ለማግኘት ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣+በፈረሶች ለሚመኩ፣+ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎችናብርቱ በሆኑ የጦር ፈረሶች* ለሚታመኑ ወዮላቸው! ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ ተስፋ አያደርጉም፤ይሖዋንም አይሹም።
6 ምክንያቱም ይሖዋ የሶርያውያን ሰፈር የጦር ሠረገሎችን ድምፅ፣ የፈረሶችን ድምፅና የታላቅ ሠራዊት ድምፅ እንዲሰማ አድርጎ ነበር።+ በመሆኑም እርስ በርሳቸው “የእስራኤል ንጉሥ እኛን ለመውጋት የሂታውያንንና የግብፅን ነገሥታት ቀጥሮብናል!” ተባባሉ። 7 እነሱም ወዲያውኑ ተነስተው በምሽት ሸሹ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም ሰፈሩን እንዳለ ትተው ሕይወታቸውን* ለማዳን እግሬ አውጪኝ አሉ።
31 እርዳታ ለማግኘት ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፣+በፈረሶች ለሚመኩ፣+ብዛት ባላቸው የጦር ሠረገሎችናብርቱ በሆኑ የጦር ፈረሶች* ለሚታመኑ ወዮላቸው! ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ ተስፋ አያደርጉም፤ይሖዋንም አይሹም።