ምሳሌ
21 የንጉሥ ልብ በይሖዋ እጅ እንዳለ ጅረት ነው።+
እሱ ደስ ወዳሰኘው አቅጣጫ ሁሉ ይመራዋል።+
3 መሥዋዕት ከማቅረብ ይልቅ
ትክክልና ፍትሐዊ የሆነ ነገር ማድረግ ይሖዋን ይበልጥ ደስ ያሰኘዋል።+
4 ትዕቢተኛ ዓይንና እብሪተኛ ልብ
የክፉዎች መብራት ናቸው፤ ደግሞም ኃጢአት ናቸው።+
7 ክፉዎች ፍትሕን ማስፈን ስለማይፈልጉ
የሚፈጽሙት ግፍ ጠራርጎ ይወስዳቸዋል።+
8 የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፤
የንጹሕ ሰው ሥራ ግን ቀና ነው።+
12 ጻድቅ የሆነው አምላክ፣ የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤
ክፉዎችንም ይጠፉ ዘንድ ይገለብጣቸዋል።+
13 ችግረኛው የሚያሰማውን ጩኸት ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን ሁሉ፣
እሱ ራሱ ይጮኻል፤ መልስም አያገኝም።+
15 ጻድቅ ፍትሐዊ ነገር ማድረግ ያስደስተዋል፤+
ክፉ ድርጊት ለሚፈጽሙ ግን አስከፊ ነገር ነው።
16 ከማስተዋል መንገድ ወጥቶ የሚባዝን ሰው፣
በሞት ከተረቱት ጋር ያርፋል።+
18 ክፉ ሰው ለጻድቅ ቤዛ ነው፤
ከዳተኛ የሆነ ሰውም በቅን ሰው ፋንታ ይወሰዳል።+
21 ጽድቅንና ታማኝ ፍቅርን የሚከታተል ሰው ሁሉ
ሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል።+
24 በእብሪት የመሰለውን የሚያደርግ ሰው
እብሪተኛና ጉረኛ ይባላል።+
25 ሰነፍ ሰው ምኞቱ ይገድለዋል፤
እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።+
26 ቀኑን ሙሉ በስግብግብነት ሲመኝ ይውላል፤
ጻድቅ ግን ምንም ሳይሰስት ይሰጣል።+
27 የክፉ ሰው መሥዋዕት አስጸያፊ ነው።+
በክፉ ዓላማ ተነሳስቶ* ሲያቀርብማ ምንኛ የከፋ ይሆናል!
30 ይሖዋን የሚጻረር ጥበብ፣ ማስተዋልም ሆነ ምክር ከንቱ ነው።+