ምሳሌ
2 ሀብታምንና ድሃን የሚያመሳስላቸው ነገር አለ፦*
ሁለቱንም የፈጠረው ይሖዋ ነው።+
3 ብልህ ሰው አደጋ ሲያይ ይሸሸጋል፤
ተሞክሮ የሌለው ግን ዝም ብሎ ይሄዳል፤ መዘዙንም* ይቀበላል።
4 ትሕትናና ይሖዋን መፍራት
ሀብት፣ ክብርና ሕይወት ያስገኛል።+
7 ሀብታም ድሃን ይገዛል፤
ተበዳሪም የአበዳሪው ባሪያ ነው።+
11 ንጹሕ ልብ የሚወድና ንግግሩ ለዛ ያለው ሰው፣
የንጉሥ ወዳጅ ይሆናል።+
12 የይሖዋ ዓይኖች እውቀትን ይጠብቃሉ፤
የከዳተኛን ቃል ግን ይሽራል።+
13 ሰነፍ “ውጭ አንበሳ አለ!
አደባባይ ላይ እገደላለሁ!” ይላል።+
ይሖዋ ያወገዘው ሰው እዚያ ውስጥ ይወድቃል።
17 እውቀቴን በሙሉ ልብ እንድትቀበል+
ጆሮህን አዘንብል፤ የጥበበኞችንም ቃል አዳምጥ፤+
18 ምንጊዜም ይህ ቃል ሙሉ በሙሉ በከንፈሮችህ ላይ እንዲሆን+
ቃሉን በውስጥህ መያዝህ መልካም ነውና።+
19 በይሖዋ እንድትተማመን፣
ዛሬ እውቀት እሰጥሃለሁ።
20 ከዚህ ቀደም ምክርና
እውቀት የያዙ ሐሳቦች አልጻፍኩልህም?
21 ይህን ያደረግኩት ለላከህ ትክክለኛ ወሬ ይዘህ እንድትመለስ፣
እውነት የሆነውንና እምነት የሚጣልበትን ቃል ላስተምርህ አይደለም?
22 ድሃውን ድሃ ስለሆነ ብቻ አትዝረፈው፤+
ችግረኛውንም በከተማው በር ላይ ግፍ አትፈጽምበት፤+
23 ይሖዋ ራሱ ይሟገትላቸዋልና፤+
የሚያጭበረብሯቸውንም ሰዎች ሕይወት ያጠፋል።*
27 የምትከፍለው ካጣህ
የተኛህበት አልጋ ከሥርህ ይወሰድብሃል!
28 አባቶችህ ያደረጉትን
የጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ።+
29 በሥራው የተካነን ሰው አይተሃል?
በነገሥታት ፊት ይቆማል፤+
ተራ በሆኑ ሰዎች ፊት አይቆምም።