ምሳሌ
3 የእሱ ጣፋጭ ምግብ አያስጎምጅህ፤
ምግቡ አታላይ ነውና።
4 ሀብት ለማግኘት አትልፋ።+
ይህን ትተህ በማስተዋል ተመላለስ።*
“ብላ፣ ጠጣ” ይልሃል፤ የሚናገረው ግን ከልቡ አይደለም።*
8 የበላሃትን ቁራሽ ምግብ ታስመልሳለህ፤
የተናገርካቸው የምስጋና ቃላትም ከንቱ ይሆናሉ።
10 የጥንቱን የወሰን ምልክት ከቦታው አታንቀሳቅስ፤+
ደግሞም አባት የሌላቸውን ልጆች መሬት አትያዝ።
12 ልብህን ለተግሣጽ፣
ጆሮህንም ለእውቀት ቃል ስጥ።
በበትር ብትመታው አይሞትም።
15 ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣
የእኔ ልብ ሐሴት ያደርጋል።+
16 ከንፈሮችህ ትክክል የሆነውን ሲናገሩ
ውስጤ ደስ ይለዋል።*
17 ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤+
ከዚህ ይልቅ ቀኑን ሙሉ ይሖዋን በመፍራት ተመላለስ፤+
18 እንዲህ ብታደርግ የወደፊት ሕይወትህ የተሳካ ይሆናል፤+
ተስፋህም ከንቱ አይሆንም።
19 ልጄ ሆይ፣ አዳምጥ፤ ጥበበኛም ሁን፤
ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ምራ።
22 የወለደህን አባትህን ስማ፤
እናትህንም ስላረጀች አትናቃት።+
24 የጻድቅ አባት ደስ ይለዋል፤
ጥበበኛ ልጅ የወለደ ሁሉ በልጁ ሐሴት ያደርጋል።
25 አባትህና እናትህ ሐሴት ያደርጋሉ፤
አንተን የወለደችም ደስ ይላታል።
26 ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፤
ዓይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።+
28 እንደ ዘራፊ ታደባለች፤+
ታማኝ ያልሆኑ ወንዶችን ቁጥር ታበዛለች።
29 ዋይታ የማን ነው? ጭንቀት የማን ነው?
ጠብ የማን ነው? እሮሮ የማን ነው?
ያለምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን ቅላት* የማን ነው?
31 በብርጭቆ ውስጥ ሲያንጸባርቅ፣
እየጣፈጠም ሲወርድ በወይን ጠጅ ቅላት ዓይንህ አይማረክ፤
32 በመጨረሻ እንደ እባብ ይናደፋልና፤
እንደ እፉኝትም መርዙን ይረጫል።
33 ዓይኖችህ እንግዳ ነገር ያያሉ፤
ልብህም ጠማማ ነገር ይናገራል።+
34 በባሕር መካከል እንደተኛ፣
በመርከብ ምሰሶም ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ።
35 እንዲህ ትላለህ፦ “መቱኝ፤ ሆኖም አልተሰማኝም።*
ደበደቡኝ፤ ሆኖም አልታወቀኝም።
ተጨማሪ መጠጥ እጠጣ ዘንድ*
የምነቃው መቼ ነው?”+