መዝሙር 31:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እኔ በድንጋጤ ተውጬ “ከፊትህ መጥፋቴ ነው” አልኩ።+ አንተ ግን እርዳታ ለማግኘት በጮኽኩ ጊዜ ልመናዬን ሰማህ።+ መዝሙር 40:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ተስፋዬን ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ ጣልኩ፤*እሱም ጆሮውን ወደ እኔ አዘነበለ፤* ለእርዳታ ያሰማሁትንም ጩኸት ሰማ።+ ዮናስ 2:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 እንዲህም አለ፦ “ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ይሖዋ ተጣራሁ፤ እሱም መለሰልኝ።+ በመቃብር* ጥልቅ* ውስጥ ሆኜ እርዳታ ለማግኘት ጮኽኩ።+ አንተም ድምፄን ሰማህ።