መዝሙር 54:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እነሆ፣ አምላክ ረዳቴ ነው፤+ይሖዋ እኔን* ከሚደግፉ ጋር ነው። ኢሳይያስ 50:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ሆኖም ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ይረዳኛል።+ ስለዚህ አልዋረድም። ከዚህም የተነሳ ፊቴን እንደ ባልጩት አደረግኩ፤+ለኀፍረት እንደማልዳረግም አውቃለሁ። ዕብራውያን 13:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ስለዚህ በሙሉ ልብ “ይሖዋ* ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።+